The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Clot [Al-Alaq] - Amharic translation
Surah The Clot [Al-Alaq] Ayah 19 Location Maccah Number 96
አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡{1}
ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡
አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤
ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡
ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡
በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡
ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡
መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡
ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤
አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤
ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤
አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤
አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን?
ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡
ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡
ሸንጎውንም ይጥራ፡፡
(እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡
ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡ {1}