The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe cave [Al-Kahf] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 22
Surah The cave [Al-Kahf] Ayah 110 Location Maccah Number 18
سَيَقُولُونَ ثَلَٰثَةٞ رَّابِعُهُمۡ كَلۡبُهُمۡ وَيَقُولُونَ خَمۡسَةٞ سَادِسُهُمۡ كَلۡبُهُمۡ رَجۡمَۢا بِٱلۡغَيۡبِۖ وَيَقُولُونَ سَبۡعَةٞ وَثَامِنُهُمۡ كَلۡبُهُمۡۚ قُل رَّبِّيٓ أَعۡلَمُ بِعِدَّتِهِم مَّا يَعۡلَمُهُمۡ إِلَّا قَلِيلٞۗ فَلَا تُمَارِ فِيهِمۡ إِلَّا مِرَآءٗ ظَٰهِرٗا وَلَا تَسۡتَفۡتِ فِيهِم مِّنۡهُمۡ أَحَدٗا [٢٢]
22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ስለ እነርሱ የተወሰኑ ቡድኖች በጥርጣሬ) «ሶስት ናቸው አራተኛው ውሻቸው ነው።» ይላሉ:: (ሌሎች ቡድኖች) «አምስት ናቸው ስድስተኛው ውሻቸው ነው።» ይላሉ። በሩቅ ወርዋሪዎች ሆነው (ባላወቁት አለም) ሲገምቱ። (ሶስተኛው ቡድን ደግሞ) «ሰባት ናቸው ስምንተኛቸው ውሻቸው ነዉ።» ይላሉ:: «ጌታዬ ብቻ ቁጥራቸውን አዋቂ ነው:: ጥቂት ሰው እንጂ አያውቃቸዉም።» በላቸው:: እናም በእነርሱ ነገር ግልጽን ክርክር እንጂ ጠልቀህ አትከራከር:: በእነርሱም ጉዳይ ከመጽሐፉ ሰዎች አንድንም አትጠይቅ::