عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The Cow [Al-Baqara] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 187

Surah The Cow [Al-Baqara] Ayah 286 Location Madanah Number 2

أُحِلَّ لَكُمۡ لَيۡلَةَ ٱلصِّيَامِ ٱلرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَآئِكُمۡۚ هُنَّ لِبَاسٞ لَّكُمۡ وَأَنتُمۡ لِبَاسٞ لَّهُنَّۗ عَلِمَ ٱللَّهُ أَنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَخۡتَانُونَ أَنفُسَكُمۡ فَتَابَ عَلَيۡكُمۡ وَعَفَا عَنكُمۡۖ فَٱلۡـَٰٔنَ بَٰشِرُوهُنَّ وَٱبۡتَغُواْ مَا كَتَبَ ٱللَّهُ لَكُمۡۚ وَكُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَكُمُ ٱلۡخَيۡطُ ٱلۡأَبۡيَضُ مِنَ ٱلۡخَيۡطِ ٱلۡأَسۡوَدِ مِنَ ٱلۡفَجۡرِۖ ثُمَّ أَتِمُّواْ ٱلصِّيَامَ إِلَى ٱلَّيۡلِۚ وَلَا تُبَٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمۡ عَٰكِفُونَ فِي ٱلۡمَسَٰجِدِۗ تِلۡكَ حُدُودُ ٱللَّهِ فَلَا تَقۡرَبُوهَاۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ ءَايَٰتِهِۦ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ [١٨٧]

187. (ሙስሊሞች ሆይ!) በፆም ሌሊት ከሚስቶቻችሁ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ተፈቀደላችሁ:: እነርሱ ለእናንተ ልብሶች ናቸው:: እናንተም ለእነርሱ ልብሶች ናችሁና:: አላህ በዚህ ረገድ ነፍሶቻችሁን በማታለል ላይ መሆናችሁን ያውቃል::በእናንተም ላይ ተመለሰላችሁ፡፡ ከእናንተም ይቅርታ አደረገ፡፡ አሁን ተገናኙዋቸው፡፡ አላህም ለናንተ የጻፈላችሁን ነገር (ልጅን) ፈልጉ፡፡ ነጩ የንጋት ገመድ ከጥቁሩ የሌሊት ገመድ ለእናንተ እስከሚገለጽላችሁ ድረስ ብሉ:: ጠጡም:: ከዚያም ፆምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ:: እናንተ በመስጊዶች ተቀማጮች ኢዕቲካፍ ላይ ስትሆኑ ግን ሚስቶቻችሁን አትገናኙዋቸው:: ይህች የአላህ ህግጋት ናትና ለመተላለፍ አትቅረቧት:: ልክ እንደዚሁ አላህ አናቅጽን ለሰዎች ያብራራል:: እነርሱ የተከለከሉትን ሊጠነቀቁ ይከጅላልና::