The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Cow [Al-Baqara] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 196
Surah The Cow [Al-Baqara] Ayah 286 Location Madanah Number 2
وَأَتِمُّواْ ٱلۡحَجَّ وَٱلۡعُمۡرَةَ لِلَّهِۚ فَإِنۡ أُحۡصِرۡتُمۡ فَمَا ٱسۡتَيۡسَرَ مِنَ ٱلۡهَدۡيِۖ وَلَا تَحۡلِقُواْ رُءُوسَكُمۡ حَتَّىٰ يَبۡلُغَ ٱلۡهَدۡيُ مَحِلَّهُۥۚ فَمَن كَانَ مِنكُم مَّرِيضًا أَوۡ بِهِۦٓ أَذٗى مِّن رَّأۡسِهِۦ فَفِدۡيَةٞ مِّن صِيَامٍ أَوۡ صَدَقَةٍ أَوۡ نُسُكٖۚ فَإِذَآ أَمِنتُمۡ فَمَن تَمَتَّعَ بِٱلۡعُمۡرَةِ إِلَى ٱلۡحَجِّ فَمَا ٱسۡتَيۡسَرَ مِنَ ٱلۡهَدۡيِۚ فَمَن لَّمۡ يَجِدۡ فَصِيَامُ ثَلَٰثَةِ أَيَّامٖ فِي ٱلۡحَجِّ وَسَبۡعَةٍ إِذَا رَجَعۡتُمۡۗ تِلۡكَ عَشَرَةٞ كَامِلَةٞۗ ذَٰلِكَ لِمَن لَّمۡ يَكُنۡ أَهۡلُهُۥ حَاضِرِي ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ [١٩٦]
196. ሐጅንና ዑምራን ለአላህ ብቻ ብላችሁ በትክክል ፈጽሙ:: ከጀመራችሁ በኋላ ብትታጉዱም ከመስዋአት የቻላችሁትን መሰዋት አለባችሁ:: መስዋእቱ ከመታረጃው ስፍራ እስኪደርስ ድረስም ራሶቻችሁን አትላጩ:: ከናንተም ውስጥ በሐጅ ላይ ሁኖ የታመመ ወይም በራስ ቅሉ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሰው ቢላጭ ከመፆም ወይም መስዋዕትን ቤዛ መስጠት አለበት:: ጸጥታም ባገኛችሁ ጊዜ እስከ ሐጅ መፈጸሚያ ቀን ድረስ በዑምራ አስቀድሞ በመፈጸም የተገላገለ ሰው ከመስዋእቱ የተገራውን (የቻለዉን) መሰዋት አለበት:: ያላገኘም ሰው ሶስትን ቀናት በሐጅ (ወራት) ላይ ሰባትንም ቀናት ደግሞ በተመለሳችሁ ጊዜ መፆም አለበት:: እነዚህ ሙሉ አስር (ቀናት) ናቸው:: ይህም (ህግ) ቤተሰቦቹ ከቅዱሱ መስጊድ አቅራቢያ ላልሆኑ ነው:: አላህንም ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ መሆኑንም እወቁ።