The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Cow [Al-Baqara] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 235
Surah The Cow [Al-Baqara] Ayah 286 Location Madanah Number 2
وَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ فِيمَا عَرَّضۡتُم بِهِۦ مِنۡ خِطۡبَةِ ٱلنِّسَآءِ أَوۡ أَكۡنَنتُمۡ فِيٓ أَنفُسِكُمۡۚ عَلِمَ ٱللَّهُ أَنَّكُمۡ سَتَذۡكُرُونَهُنَّ وَلَٰكِن لَّا تُوَاعِدُوهُنَّ سِرًّا إِلَّآ أَن تَقُولُواْ قَوۡلٗا مَّعۡرُوفٗاۚ وَلَا تَعۡزِمُواْ عُقۡدَةَ ٱلنِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبۡلُغَ ٱلۡكِتَٰبُ أَجَلَهُۥۚ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا فِيٓ أَنفُسِكُمۡ فَٱحۡذَرُوهُۚ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٞ [٢٣٥]
235. (ወንዶች ሆይ!) ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች የጋብቻ (አሽሙር) ፍንጭ በመስጠታችሁ ወይም እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ በውስጣችሁ በማሰባችሁ ምክንያት በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ እናንተ በእርግጥ እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ እንደምታስተናግዱ ቀድሞውኑ ያውቃል:: ስለዚህ (አሽሙር) ፍንጭ መስጠትንና ማሰብን ፈቀደላችሁ:: ግና በሕግ የታወቀን ጨዋ ንግግር የምትነጋገሩ ካልሆናችሁ በስተቀር የተፃፈው የኢዳ ጊዜው እስከሚደርስ ድረስ ለትዳር እንደምትፈልጓቸው በሚስጥር ቃል አትግቡላቸው:: ጋብቻን ለመዋዋልም ቁርጥ ሀሳብ አታድርጉ:: አላህ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉን ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑን እወቁ:: ተጠንቀቁም፤ አላህ መሀሪና ታጋሽ መሆኑንም እወቁ::