عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The Pilgrimage [Al-Hajj] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 5

Surah The Pilgrimage [Al-Hajj] Ayah 78 Location Maccah Number 22

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِن كُنتُمۡ فِي رَيۡبٖ مِّنَ ٱلۡبَعۡثِ فَإِنَّا خَلَقۡنَٰكُم مِّن تُرَابٖ ثُمَّ مِن نُّطۡفَةٖ ثُمَّ مِنۡ عَلَقَةٖ ثُمَّ مِن مُّضۡغَةٖ مُّخَلَّقَةٖ وَغَيۡرِ مُخَلَّقَةٖ لِّنُبَيِّنَ لَكُمۡۚ وَنُقِرُّ فِي ٱلۡأَرۡحَامِ مَا نَشَآءُ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗى ثُمَّ نُخۡرِجُكُمۡ طِفۡلٗا ثُمَّ لِتَبۡلُغُوٓاْ أَشُدَّكُمۡۖ وَمِنكُم مَّن يُتَوَفَّىٰ وَمِنكُم مَّن يُرَدُّ إِلَىٰٓ أَرۡذَلِ ٱلۡعُمُرِ لِكَيۡلَا يَعۡلَمَ مِنۢ بَعۡدِ عِلۡمٖ شَيۡـٔٗاۚ وَتَرَى ٱلۡأَرۡضَ هَامِدَةٗ فَإِذَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡهَا ٱلۡمَآءَ ٱهۡتَزَّتۡ وَرَبَتۡ وَأَنۢبَتَتۡ مِن كُلِّ زَوۡجِۭ بَهِيجٖ [٥]

5. ሰዎች ሆይ! ከሞት በኋላ ከመቀስቀስ በመጠራጠር ጉዳይ እንደ ሆናችሁ የመጀመሪያውን (አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ። እኛም) ከአፈር ፈጠርናችሁ:: ከዚያ ከፍትወት ጠብታ፤ ከዚያም ከረጋ ደም፤ ከዚያም ከቁራጭ ስጋ ፍጥረትዋ ሙሉ ከሆነችና ሙሉ ካልሆነች (ችሎታችንን) ለእናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ። የምንሻውንም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በማህጸን ውስጥ እናረጋዋለን። ከዚያም ህፃን ሆናችሁ እናወጣችኋለን:: ከዚያም ሙሉ ጥንካሪያችሁን ትደርሱ ዘንድ (እናሳድጋችኋለን):: ከናንተም መካከል በወጣትነቱ የሚሞት ሰው አለ:: ከናንተም መካከል ከዕውቀት በኋላ ምንንም ላያውቅ ወደ ጃጀ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አለ:: ምድርንም ደረቅ ሆና ታያታለህ:: በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ ትላወሳለች \ትነቃነቃለች\:: ትነፋለችም:: ውበት ካለው የእጽዋት አይነት ሁሉ ታበቅላለችም።