The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Women [An-Nisa] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 102
Surah The Women [An-Nisa] Ayah 176 Location Madanah Number 4
وَإِذَا كُنتَ فِيهِمۡ فَأَقَمۡتَ لَهُمُ ٱلصَّلَوٰةَ فَلۡتَقُمۡ طَآئِفَةٞ مِّنۡهُم مَّعَكَ وَلۡيَأۡخُذُوٓاْ أَسۡلِحَتَهُمۡۖ فَإِذَا سَجَدُواْ فَلۡيَكُونُواْ مِن وَرَآئِكُمۡ وَلۡتَأۡتِ طَآئِفَةٌ أُخۡرَىٰ لَمۡ يُصَلُّواْ فَلۡيُصَلُّواْ مَعَكَ وَلۡيَأۡخُذُواْ حِذۡرَهُمۡ وَأَسۡلِحَتَهُمۡۗ وَدَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوۡ تَغۡفُلُونَ عَنۡ أَسۡلِحَتِكُمۡ وَأَمۡتِعَتِكُمۡ فَيَمِيلُونَ عَلَيۡكُم مَّيۡلَةٗ وَٰحِدَةٗۚ وَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ إِن كَانَ بِكُمۡ أَذٗى مِّن مَّطَرٍ أَوۡ كُنتُم مَّرۡضَىٰٓ أَن تَضَعُوٓاْ أَسۡلِحَتَكُمۡۖ وَخُذُواْ حِذۡرَكُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ أَعَدَّ لِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٗا مُّهِينٗا [١٠٢]
102.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ) በጦርነት ላይ በመካከላቸው በሆንክና ሶላትን ለእነርሱ ባሰገድካቸው ጊዜ ከእነርሱ አንዱ ቡድን ካንተ ጋር ይቁም:: መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ:: ሱጁድ ባደረጉ ጊዜ ከበስተኋላችሁ ይሁኑ:: ከዚያም እነዚያ ቡድኖች ወደ ግንባር ይሂዱና ያልሰገዱት ሌሎች ቡድኖች ይምጡ :: ከዚያም ካንተ ጋር ይስገዱ:: ጥንቃቄያቸውንና መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ:: እነዚያ በአላህ የካዱት ከትጥቅና ስንቃችሁ ብትዘናጉና በአንድ ጊዜ ቢወሯችሁ ይመኛሉ:: ዝናብ አውኳችሁ ወይም በሽተኛ ሆናችሁ ትጥቃችሁን ብታስቀምጡ በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: ጥንቃቄ አድርጉ:: አላህ ለካሐዲያን ሁሉ አዋራጅን ቅጣት አዘጋጀ::