عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The Women [An-Nisa] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 12

Surah The Women [An-Nisa] Ayah 176 Location Madanah Number 4

۞ وَلَكُمۡ نِصۡفُ مَا تَرَكَ أَزۡوَٰجُكُمۡ إِن لَّمۡ يَكُن لَّهُنَّ وَلَدٞۚ فَإِن كَانَ لَهُنَّ وَلَدٞ فَلَكُمُ ٱلرُّبُعُ مِمَّا تَرَكۡنَۚ مِنۢ بَعۡدِ وَصِيَّةٖ يُوصِينَ بِهَآ أَوۡ دَيۡنٖۚ وَلَهُنَّ ٱلرُّبُعُ مِمَّا تَرَكۡتُمۡ إِن لَّمۡ يَكُن لَّكُمۡ وَلَدٞۚ فَإِن كَانَ لَكُمۡ وَلَدٞ فَلَهُنَّ ٱلثُّمُنُ مِمَّا تَرَكۡتُمۚ مِّنۢ بَعۡدِ وَصِيَّةٖ تُوصُونَ بِهَآ أَوۡ دَيۡنٖۗ وَإِن كَانَ رَجُلٞ يُورَثُ كَلَٰلَةً أَوِ ٱمۡرَأَةٞ وَلَهُۥٓ أَخٌ أَوۡ أُخۡتٞ فَلِكُلِّ وَٰحِدٖ مِّنۡهُمَا ٱلسُّدُسُۚ فَإِن كَانُوٓاْ أَكۡثَرَ مِن ذَٰلِكَ فَهُمۡ شُرَكَآءُ فِي ٱلثُّلُثِۚ مِنۢ بَعۡدِ وَصِيَّةٖ يُوصَىٰ بِهَآ أَوۡ دَيۡنٍ غَيۡرَ مُضَآرّٖۚ وَصِيَّةٗ مِّنَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَلِيمٞ [١٢]

12. ለእናንተም ሚስቶቻችሁ ከተውት ንብረት ለእነርሱ ልጅ ካልኖራቸው ግማሹ አላችሁ:: ለእነርሱም ልጅ ቢኖራቸው ከተውት ሀብት ከአራት አንድ አላችሁ :: (ይህም) በእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከእዳ ክፍያ በኋላ ነው:: ለእናንተም ልጅ ከሌላችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ (ለሚስቶቻችሁ) አንድ አራተኛ አላቸው። ለእናንተም ልጅ ባይኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ (ለሚስቶቻችሁ) ከስምንት አንድ አላቸው:: (ይህም) ከምትናዘዙበት ኑዛዜ ወይም ከእዳ ክፍያ በኋላ ነው:: ወላጆችም ልጅም የሌለውና የጎን ወራሾች የሚወርሱት ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ ለእርሱም (ለሟቹ) ከእናቱ በኩል ብቻ የሆኑ ወንድም ወይም እህት ቢኖሩት ከሁለቱ ለእያንደንዳቸው ከስድስት አንድ አላቸው:: ከአንድ የበዙ ቢሆኑ ደግሞ በሲሶው ላይ ተጋሪዎች ናቸው:: ይህም ወራሾቹን የማይጎዳ ሆኖ ከእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከእዳ በኋላ ነው:: ከአላህም የሆነን ኑዛዜ ያዛችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ቻይ ነውና።