عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The Women [An-Nisa] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 6

Surah The Women [An-Nisa] Ayah 176 Location Madanah Number 4

وَٱبۡتَلُواْ ٱلۡيَتَٰمَىٰ حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغُواْ ٱلنِّكَاحَ فَإِنۡ ءَانَسۡتُم مِّنۡهُمۡ رُشۡدٗا فَٱدۡفَعُوٓاْ إِلَيۡهِمۡ أَمۡوَٰلَهُمۡۖ وَلَا تَأۡكُلُوهَآ إِسۡرَافٗا وَبِدَارًا أَن يَكۡبَرُواْۚ وَمَن كَانَ غَنِيّٗا فَلۡيَسۡتَعۡفِفۡۖ وَمَن كَانَ فَقِيرٗا فَلۡيَأۡكُلۡ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ فَإِذَا دَفَعۡتُمۡ إِلَيۡهِمۡ أَمۡوَٰلَهُمۡ فَأَشۡهِدُواْ عَلَيۡهِمۡۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ حَسِيبٗا [٦]

6. (ሙስሊሞች ሆይ!) የቲሞችን ለጋብቻ እስከደረሱ ድረስ ፈትኗቸው:: ከእነርሱም ብልህነትን ብታውቁ ገንዘቦቻቸውን ስጧቸው:: በማባከንና ማደጋቸውን በመሽቀዳደም ገንዘቦቻቸውን አትብሉባቸው:: (ከአሳዳጊዎቹ መካከል) ሀብታም የሆነ ሰው ከገንዘቦቻቸው (ቅንጣት ያህል እንኳን ከመቅረብ) ይከልከል:: ደሃ የሆነ ሰዉም ቢሆን ለድካሙ ብቻ በአግባቡ ይብላ:: ገንዘቦቻቸውን ወደ እነርሱ በሰጣችሁም ጊዜ በእነርሱ ላይ አስመስክሩ:: በተጠባባቂነትም አላህ በቂ ነው::