The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesMuhammad [Muhammad] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 15
Surah Muhammad [Muhammad] Ayah 38 Location Madanah Number 47
مَّثَلُ ٱلۡجَنَّةِ ٱلَّتِي وُعِدَ ٱلۡمُتَّقُونَۖ فِيهَآ أَنۡهَٰرٞ مِّن مَّآءٍ غَيۡرِ ءَاسِنٖ وَأَنۡهَٰرٞ مِّن لَّبَنٖ لَّمۡ يَتَغَيَّرۡ طَعۡمُهُۥ وَأَنۡهَٰرٞ مِّنۡ خَمۡرٖ لَّذَّةٖ لِّلشَّٰرِبِينَ وَأَنۡهَٰرٞ مِّنۡ عَسَلٖ مُّصَفّٗىۖ وَلَهُمۡ فِيهَا مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ وَمَغۡفِرَةٞ مِّن رَّبِّهِمۡۖ كَمَنۡ هُوَ خَٰلِدٞ فِي ٱلنَّارِ وَسُقُواْ مَآءً حَمِيمٗا فَقَطَّعَ أَمۡعَآءَهُمۡ [١٥]
15. ያች አላህን ለሚፈሩ ሰዎች ቃል የተገባችው ገነት (ይህን ትመስላለች)፤ በውስጧ ሽታው ከማይለወጥ የውሃ ወንዞች፤ ጣዕሙ የማይለወጥ የወተት ወንዞች፤ ለጠጪዎች ሁሉ እጅግ ጣፋጭ የሆኑ የወይን ጠጅ ወንዞችና የንጹህ(የተነጠረ) ማር ወንዞች አሉባት:: በውስጧ ሁሉም የፍራፍሬ አይነቶች ከጌታቸዉም ምህረት ተዘጋጅተውላቸዋል:: በእነዚህ ገነቶች የሆነ እንደነዚያ እሳት ውስጥ ዘወትር እንደሚኖሩ የፈላ ውሃም እንዲጠጡ እንደሚደረጉትና ውሃዉም የሆድ ዕቃቸውን እንደሚበጣጥስባቸው ነውን? አይደለም።