The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Table Spread [Al-Maeda] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 110
Surah The Table Spread [Al-Maeda] Ayah 120 Location Madanah Number 5
إِذۡ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَى ٱبۡنَ مَرۡيَمَ ٱذۡكُرۡ نِعۡمَتِي عَلَيۡكَ وَعَلَىٰ وَٰلِدَتِكَ إِذۡ أَيَّدتُّكَ بِرُوحِ ٱلۡقُدُسِ تُكَلِّمُ ٱلنَّاسَ فِي ٱلۡمَهۡدِ وَكَهۡلٗاۖ وَإِذۡ عَلَّمۡتُكَ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَٱلتَّوۡرَىٰةَ وَٱلۡإِنجِيلَۖ وَإِذۡ تَخۡلُقُ مِنَ ٱلطِّينِ كَهَيۡـَٔةِ ٱلطَّيۡرِ بِإِذۡنِي فَتَنفُخُ فِيهَا فَتَكُونُ طَيۡرَۢا بِإِذۡنِيۖ وَتُبۡرِئُ ٱلۡأَكۡمَهَ وَٱلۡأَبۡرَصَ بِإِذۡنِيۖ وَإِذۡ تُخۡرِجُ ٱلۡمَوۡتَىٰ بِإِذۡنِيۖ وَإِذۡ كَفَفۡتُ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ عَنكَ إِذۡ جِئۡتَهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡهُمۡ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٞ [١١٠]
110. አላህ እንዲህ በሚልበት ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ላንተና ለእናትህ የዋልኩላችሁን ውለታ አስታውስ:: በሩሀል ቁዱስ (በጅብሪል) አጠነከርኩህ:: በሕጻንነትህም አድገህም ሰዎችን ማናገር ቻልክ። መጽሐፉንና ጥበብን ተውራትንና ኢንጂልንም አስተማርኩህ:: ከጭቃም የወፍ ቅርጽ ዓይነት በፈቃዴ መሥራት ቻልክ:: በሷ ውስጥ ነፈህ:: በፈቃዴም እውነተኛ በራሪ ሆነች:: እውር ሆኖ የተወለደንና ለምጻምን በፈቃዴ መፈወስ ቻልክ:: ሟችንም በፈቃዴ አስነሳህ:: የኢስራኢልንም ልጆች ግልጽ መረጃ ባመጣህላቸው ጊዜ ሊያጠቁህ ሲያስቡ አቀብኩልህ:: ከመካከላቸዉም እነዚያ በአላህ የካዱት ‹ይህ ግልጽ ድግምት ነው› አሉ:: ይህን ሁሉ ውለታዬን አስታውስ::