The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Table Spread [Al-Maeda] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 116
Surah The Table Spread [Al-Maeda] Ayah 120 Location Madanah Number 5
وَإِذۡ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَى ٱبۡنَ مَرۡيَمَ ءَأَنتَ قُلۡتَ لِلنَّاسِ ٱتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَٰهَيۡنِ مِن دُونِ ٱللَّهِۖ قَالَ سُبۡحَٰنَكَ مَا يَكُونُ لِيٓ أَنۡ أَقُولَ مَا لَيۡسَ لِي بِحَقٍّۚ إِن كُنتُ قُلۡتُهُۥ فَقَدۡ عَلِمۡتَهُۥۚ تَعۡلَمُ مَا فِي نَفۡسِي وَلَآ أَعۡلَمُ مَا فِي نَفۡسِكَۚ إِنَّكَ أَنتَ عَلَّٰمُ ٱلۡغُيُوبِ [١١٦]
116. (መልዕክተኛች ሙሐመድ ሆይ!) አላህ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ሰዎችን ‹እኔንና እናቴን ከአላህ ውጭ ሁለት አማልዕክት አድርጋችሁ ያዙን።› ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ:: ዒሳም አለ፡- «ክብርና ልዕልና ላንተ ብቻ ይሁን! ለእኔ ልለው የማይገባኝን ነገር ማለቴ ፈጽሞ አግባብ አይደለም:: ይህን ተናግሬ ከሆነም ታውቀዋለህ:: አንተ በውስጤ ያለውን ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ:: እኔ ግን ባንተ ውስጥ ያለውን አላውቅም:: አንተ ሩቅ ሚስጥራትን ሁሉ አዋቂ ነህና::