The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Table Spread [Al-Maeda] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 2
Surah The Table Spread [Al-Maeda] Ayah 120 Location Madanah Number 5
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تُحِلُّواْ شَعَٰٓئِرَ ٱللَّهِ وَلَا ٱلشَّهۡرَ ٱلۡحَرَامَ وَلَا ٱلۡهَدۡيَ وَلَا ٱلۡقَلَٰٓئِدَ وَلَآ ءَآمِّينَ ٱلۡبَيۡتَ ٱلۡحَرَامَ يَبۡتَغُونَ فَضۡلٗا مِّن رَّبِّهِمۡ وَرِضۡوَٰنٗاۚ وَإِذَا حَلَلۡتُمۡ فَٱصۡطَادُواْۚ وَلَا يَجۡرِمَنَّكُمۡ شَنَـَٔانُ قَوۡمٍ أَن صَدُّوكُمۡ عَنِ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ أَن تَعۡتَدُواْۘ وَتَعَاوَنُواْ عَلَى ٱلۡبِرِّ وَٱلتَّقۡوَىٰۖ وَلَا تَعَاوَنُواْ عَلَى ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡعُدۡوَٰنِۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ [٢]
2. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ምልክቶች ይሆኑ ዘንድ የከለከላቸውን ነገሮች የተፈቀዱ አታድርጉ። የተከበረውንም ወር በውስጡ ጦርነትን በማካሄድ አትድፈሩት:: ወደ መካ የሚነዱትን የመስዋዕት እንስሳትና የሚታበቱባቸውን ገመዶች፤ ከጌታቸው ችሮታንና ውዴታን ፈልገው ወደ ተከበረው ቤት አሳቢዎችንም በክፉ አትንኳቸው:: የሐጅን ስራ ፈጽማችሁ ባጠናቀቃችሁ ጊዜ የዱር አውሬዎችን እንደልባችሁ አድኑ:: ከተከበረው መስጊድ ስለከለከሏችሁ ሰዎችን መጥላታችሁ በእነርሱ ላይ ወሰንን እንድታልፉና ፍትህን እንድታዛቡ አይገፋፉችሁ:: በበጎ ተግባርና አላህን በመፍራት እርስ በእርስ ተባበሩ:: ኃጢአትና ወሰንን በማለፍ ግን አትተባበሩ:: አላህን በትክክል ፍሩ:: አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና::