عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The cattle [Al-Anaam] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 148

Surah The cattle [Al-Anaam] Ayah 165 Location Maccah Number 6

سَيَقُولُ ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ لَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَآ أَشۡرَكۡنَا وَلَآ ءَابَآؤُنَا وَلَا حَرَّمۡنَا مِن شَيۡءٖۚ كَذَٰلِكَ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ حَتَّىٰ ذَاقُواْ بَأۡسَنَاۗ قُلۡ هَلۡ عِندَكُم مِّنۡ عِلۡمٖ فَتُخۡرِجُوهُ لَنَآۖ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا تَخۡرُصُونَ [١٤٨]

148. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ በአላህ ያጋሩት ሰዎች አላህ በሻ ኖሮ እኛም ሆነ አባቶቻችን በአላህ ባላጋራንና አንዳችንም ነገር እርም ባላደረግን ነበር።» ይላሉ:: ልክ እነዚህ እንደ አስተባበሉህ ሁሉ እነዚያ ከበፊታቸው የነበሩ ሕዝቦችም ብርቱ ቅጣታችንን እስከ ቀመሱ ድረስ አስተባበሉ:: «ለእኛ ታስተምሩን ዘንድ ማጋራታችሁን ለመውደዱ እናንተ ዘንድ እውቀት አለን? ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አትከተሉም:: እናንተ ዋሾዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።» በላቸው።