The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe heights [Al-Araf] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 155
Surah The heights [Al-Araf] Ayah 206 Location Maccah Number 7
وَٱخۡتَارَ مُوسَىٰ قَوۡمَهُۥ سَبۡعِينَ رَجُلٗا لِّمِيقَٰتِنَاۖ فَلَمَّآ أَخَذَتۡهُمُ ٱلرَّجۡفَةُ قَالَ رَبِّ لَوۡ شِئۡتَ أَهۡلَكۡتَهُم مِّن قَبۡلُ وَإِيَّٰيَۖ أَتُهۡلِكُنَا بِمَا فَعَلَ ٱلسُّفَهَآءُ مِنَّآۖ إِنۡ هِيَ إِلَّا فِتۡنَتُكَ تُضِلُّ بِهَا مَن تَشَآءُ وَتَهۡدِي مَن تَشَآءُۖ أَنتَ وَلِيُّنَا فَٱغۡفِرۡ لَنَا وَٱرۡحَمۡنَاۖ وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡغَٰفِرِينَ [١٥٥]
155. ሙሳም ከህዝቦቹ መካከል ለቀጠሯችን ሰባ ሰዎችን መረጠ:: ከዚያ ብርቱ የምድር እንቅጥቃጤ በደረሰባቸው ጊዜ ሙሳ አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! ብትፈልግ ኖሮ ከአሁን በፊት ባጠፋሀቸው ነበር:: እኔንም ባጠፋኸኝ ነበር:: ከእኛ መሀከል ቂሎቹ በሠሩት ጥፋት ታጠፋናለህን? ፈተናይቱ የአንተ ፈተና እንጂ ሌላ አይደለችም:: በእርሷ የምትሻውን ታሳስታለህ። የምትሻውንም ታቀናለህ:: አንተ ረዳታችን ነህና:: ለእኛ ምህረት አድርግልን። እዘንልንም:: አንተ ከመሀሪዎች ሁሉ በላጭ ነህና::