The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe cloaked one [Al-Muddathir] - Amharic translation - Africa Academy - Ayah 31
Surah The cloaked one [Al-Muddathir] Ayah 56 Location Maccah Number 74
وَمَا جَعَلۡنَآ أَصۡحَٰبَ ٱلنَّارِ إِلَّا مَلَٰٓئِكَةٗۖ وَمَا جَعَلۡنَا عِدَّتَهُمۡ إِلَّا فِتۡنَةٗ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ لِيَسۡتَيۡقِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَيَزۡدَادَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِيمَٰنٗا وَلَا يَرۡتَابَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَلِيَقُولَ ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ وَٱلۡكَٰفِرُونَ مَاذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلٗاۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَمَا يَعۡلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَۚ وَمَا هِيَ إِلَّا ذِكۡرَىٰ لِلۡبَشَرِ [٣١]
31. የእሳትን ዘበኞች መላዕክት እንጂ ሌላ አላደረግንም:: ቁጥራቸውንም ለእነዚያ በአላህ ለካዱት ሰዎች መፈተኛ እንጂ ለሌላ አላደረግንም:: እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች እንዲያረጋግጡ፤ እነዚያም በትክክል ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፤ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምዕመናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፤ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አስመሳዮችና ከሓዲያን «አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል?» እንዲሉ እንጂ (አላደረግንም):: ልክ እንደዚሁ አላህ የሚፈልገውን ያጠማል:: የሚፈልገውንም ያቀናል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህንም ሰራዊት ልክ ከእርሱ በስተቀር ማንም አያውቅም:: የሰቀር እሳት ለሰዎች መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም::