عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The earthquake [Al-Zalzala] - Amharic Translation - Africa Academy

Surah The earthquake [Al-Zalzala] Ayah 8 Location Madanah Number 99

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምድር በኃይል መንቀጥቀጧን በተንቀጠቀች ጊዜ፤

ምድርም ሸክሞቿን ባወጣች ጊዜ፤

ሰዉም "ምን ሆነች?" ባለ ጊዜ፤

በዚያ ቀን ወሬዎቿን ትናገራለች::

ጌታህ ለእርሷ አሳውቋታልና፤

በዚያ ቀን ሰዎች ሁሉ ስራዎቻቸውን እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ እንደየስራቸው የተበታተኑ ሆነው ከየመቃብራቸው ወደ መቆሚያው ስፍራ ይመለሳሉ::

የብናኝን ክብደት ያህል መልካም የሰራ ሰው ያገኘዋል::

የብናኝን ክብደት ያህል ክፋት የሰራ ሰውም ያገኘዋል::